የስነ-ልቦና ቁስል ማገገም (trauma healing) አና ወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃትና ትንኮሳን መከላከል (PSEAH) ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ) ከዩ. ኤን. ትረስት ፈንድ በተገኘችው የገንዘብ ድጋፍ ከሰኔ 17-18, 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ማዶ ሆቴል ለሁለት ቀናት የቆየ የስነ-ልቦና ቁስል ማገገም (trauma healing) እና ወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃትና ትንኮሳን መከላከል (PSEAH) ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመጀመሪያ ደረጃ አገልግሎት ሰጪዎች እና ለሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተሰጥቷል።
ሥልጠናው ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችን እና ሴት ልጆችን ማዕከል ያደረገ ብሎም ደህንነታቸው በተጠበቀ እና ሥነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጋቸውን ዕውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ ያለመ ሲሆን በተጨማሪም በስራ ቦት አካባቢ ሰለሚፈጸም ወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃትና ትንኮሳን መከላከል ዙሪያ መሠረታዊ ጽንሰ-ሐሳቦች በስፋት ገለጻ የተሰጠ ሲሆን፣ የሪፖርት ማቅረቢያ ሥርዓቶችን፣ በተቋማት ውስጥ ሊኖሩ ስለሚገቡ የደህንነት መከታተያ ሥርዓቶች፣ አና ለሴቶች እና ሴት ልጆች መሰጠት ሰልሚገባው ጥበቃ፣ የሪፖርት መቀበያ መንገዶችን ሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የአገልግሎት ሰጪዎች ቁልፍ ኃላፊነቶች በዝርዝር ተዳሰዋል።
በስልጠናው ተሳታፊዎች ጉዳት ደርሶባቸው በማገገም ላይ ያሉ ሴቶችን እና ሴት ልጆችን ማዕከል ያደረገ እና የስነ-ልቦና ቁስል የገጠማቸው ሴቶች ካሉበት ችግር እንዲወጡ ማገዝ ላይ የተመሠረተ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተሳታፊዎች ያላቸውን ግንዛቤ አሳድገዋል። በተጨማሪም በሰነ-ለቦና የመጀመሪያ እርዳታ (PFA) ላይ ተግባራዊ ክህሎታቸውን በማጠናከር እና በተጠያቂነትም
ዕውቀትና ክህሎት ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዳሳዩ አመልክቷል። በተጨማሪም የPSEAH ሪፖርት ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ የስነ-ልቦና ቁስል ማገገም ሂደት ወቀት የባለሙያ ተግባቦት እና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች በዕለት ዕለት የአገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ ለማካተት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ላይ በቂ ግንዛቤ ተፈጠሯል። በተጨማሪም የተቋማት የደህንነትና የጥበቃ ፖሊሲዎችን ለማጠናከር እና በሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ በመንግሥት ተቋማት እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ትብብርን ለማጎልበት የጋራ የተግባር ዕቅድ አዘጋጅተዋል።
በመጨረሻም ሰልጣኞች በስልጠናው የተሻለ አውቀት አንደገበዩና ያገኙትን እውቀትና ልምድ ወደተግባር ለመቀየር ያላችው ዝግጁነት ገልጸዋል። የቀንጅታዊ የቀበበሎሽ ሰርዓትን በማጠናከር ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችን እና ሴት ልጆችን ማዕከል ያደረገ፣ ተጠያቂነት የተሞላበት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የአገልግሎት ሥርዓት ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
ዓላማችን ለሴቶችና ሴት ልጆች ምቹ የሆነች ኢትዬጵን ማየት ነው፡፡
Share this post:
on Twitter
on Facebook
Warning: include(/home/newaethi/public_html/wp-content/plugins/dvk-social-sharing/includes/views/link-googleplus.html.php): Failed to open stream: No such file or directory in /home/newaethi/public_html/wp-content/plugins/dvk-social-sharing/includes/views/links.html.php on line 28
Warning: include(): Failed opening '/home/newaethi/public_html/wp-content/plugins/dvk-social-sharing/includes/views/link-googleplus.html.php' for inclusion (include_path='.:/opt/alt/php84/usr/share/pear:/opt/alt/php84/usr/share/php:/usr/share/pear:/usr/share/php') in /home/newaethi/public_html/wp-content/plugins/dvk-social-sharing/includes/views/links.html.php on line 28
on LinkedIn










