NEWA General Assembly – 2014 E.C.
Network of Ethiopian Women’s Associations, in collaboration with Oxfam In Ethiopia, held a consultation workshop Network of Ethiopian Women’s Associations, in collaboration with Oxfam In Ethiopia, held a consultation workshop with directors of the Gender and Planning Directorate of various government organizations on Gender Budgeting and Unpaid Care and Domestic Works. Directors of the Gender and Planning departments from various stakeholders and government organizations, discussed in detail gender budgeting and its impact on unpaid care and domestic work as well as the current gender budget allocation, gaps and solutions. One of the main points of the discussion was the non-inclusion of unpaid domestic work in the national economy and the exclusion of women, from the productive works which can be input for the macro-economy. የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ከኦክስፋም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታ በጀት አያያዝ ላይ እንዲሁም የበጀት አያያዝ በማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች እና እንክብካቤዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ በተመለከተ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ከተውጣጡ የስርዓተ-ፆታ እና እቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ጋር የመወያያ መድረክ አካሄዱ፡፡በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ እና በበጀት አያያዝ ላይ ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው መንግስታዊ ተቋማት የተውጣጡ የስርዓተ ፆታ እና ዕቅድ ክፍሎች ኃላፊዎች ተገኝተው የማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራን እንዲሁም በስርዓተ-ፆታ በጀት አመዳደብ ላይ አሁን ያለበትን ሁኔታ፣ ያሉትን ክፍተቶች እና ክፍተቶችን ለመሙላት መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተወያይተዋል፡፡ የማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ ባለው ኢኮኖሚ ምጣኔ ላይ አለመካተታቸው እና በማይከፈልባቸው ስራዎች ምክንያት በተለይም ሴቶች ከትርፋማው የኢኮኖሚ ስርአት እየተገለሉ መሆኑ የውይይት መድረኩ አንዱ ዋና ነጥብ ነበር፡፡