የስነ ፅሑፍ፣ ስነ ግጥም፣ መጣጥፍ፣ የስነ ስዕልና አጫጭር ቪዲዮዎች ውድድር​

የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ) በኢትዮጵያ የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥና የሴቶችን መብቶች ለማስጠበቅ የተቋቋመች መንግስታዊ ያልሆነች የሴቶች ደርጅቶችና ማህበራት ጥምረት ናት፡፡ ኢ.ሴ.ማ.ቅ ከምትሰራቸው ስራዎች አንዱ እና ዋነኛው ሴቶች፣ የሴት ልጆችና ወጣት ሴቶች የሚገጥሙዋቸውን ተግዳሮቶች፣ ፍላጎቶች ወደ ሚመለከታቸው መንግስታዊ ውሳኔ ሰጪ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በማቅረብ ትኩረት እንዲያገኝና የፖሊሲ ምላሽ እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡

 የሴት ልጆችንና የወጣት ሴቶች ድምፅ በማጉላት የፆታ-እኩልነትን ማረጋገጥን ህልም አድርጋ እንደምትሰራ ተቋም በስሯ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እና ተግባራትን ታክናውናለች፡፡ ከእነዚህ ተግባራት አንዱ ከቴር ደስ ሆምስ ኔዘርላንድስ (Terre des Hommes Netherlands) እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር በወጣት ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረገች ‘‘ትመራለች SheLeads”የተሰኘ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ትገኛለች፡፡

በሴቶችና እና በወጣት ሴቶች ላይ ጾታን ላይ የተመሰረተ ጥቃትን ለመከላከል የ16 ቀናት የንቅናቄ ቀናት በየአመቱ የሚካሄድ አለም አቀፍ የሲቪል ማህበረሰብ መሪ ዘመቻ ነው። በሴቶች እና በወጣት ሴቶች ላይ በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን በመቃወም ለ16 ቀናት ከሚዘልቀው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በህዳር 28 2015 ዓ. ም. የስነ ጹሁፍ፣ ስነ ግጥም፣ መጣጥፍ፣ የስነ ስዕልና አጫጭር ቪዲዮዎች ውድድር ለማድረግ ታስቧል።

በዚህ መሰረት፣ በሴት ልጆች እና ወጣት ሴቶች ላይ የሚደርስን ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን  የሚቃወምና ከንቅናቄው ጋር የተገናኙ   ግጥም፣ አጫጭር ቪዲዮ፣ መጣጥፍ እንዲሁም ስዕል በማቅረብ እንዲወዳደሩ ጥሪ ታቀርባለች።

አሸናፊው የእውቅና ሰርተፍኬት፣ ተምሳሌት መጽሐፍ፣ በኢ.ሴ.ማ.ቅ የሩብ አመት የዜና መጽሄት ላይ ስራዎቹ ይቀርባሉ፣ እንዲሁም በኢ.ሴ.ማ.ቅ ማህብራዊ ትስስር ላይ ለሰዎች ይደርሳል። ለውድድር ስራዎቻቹን መላክ የምትፈልጉ መወዳደሪያ ስራችሁን በሚከትለው ኢሜል newethiopia@gmail.com አድራሻ መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።  

ማሳሰቢያ፡ የማስረከቢያ ቀነ-ገደብ ህዳር 202015ዓ. ም. ላይ ይሆናል። ማክሰኞ ከሰዓት 1100 ሰዓት በፊት  እንዲልኩ እንጠይቃለን።