የኢትዮጵያ ሴቶች ለሰላም ግንባታ ከኢ.ሴ.ማ.ቅ ጋር በመተባበር በአማራ ክልል የማህበረሰብ ተኮር ተቋማት መሪዎችና የመንግስት አካላት ስልጠና ሰጠ

ጥቅምት 22- 23/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ለሰላም ግንባታ ከACCORD፣ ከUKFCDO እና ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት(ኢ.ሴ.ማ.ቅ) ጋር በመተባበር በአማራ ክልል በማእከላዊ ጎንደር ዞን ሶስት ወረዳወች እንዲሁም ጎንደር ከተማ የማህበረሰብ ተኮር ተቋማት መሪዎችና የመንግስት አካላት ስልጠና ሰጠ።
ስልጠናው የግጭት አስተዳደርና ሰላም ግንባታ እና ሴቶች በሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና በሚሉ አርእስቶች የተሰጠ ሲሆን የሴቶች የሰላም ግንባታ አለም አቀፍ አገር አቀፍና በአካባቢያችን ያላቸውን ተሞክሮ የስልጠናው አካል ሆኖ ቀርቧል።
ሰልጣኞች በተፈጠረላቸው ግንዛቤ ደስተኛ እንደሆኑና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ባለቤት ሆነው መፈጸም እንዳለባቸው እንዲሁም በሰላም ግንባታ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ስልጠናውን እንደአሰልጣኞች ስልጠና ቆጥረው በየአካባቢያቸው ስልጠናውን እንደሚያስቀጥሉት እና ሴቶች ባላቸው አደረጃጀት ተጠቅመው ቡና ለሰላምን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ተግባብተናል።