የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ) በሴት ልጅ ግርዛት እና ያለዕድሜ ጋብቻ ለማስቆም የማህበረሰብ ንቅናቄና ዘመቻ አካሄደች
የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ) በሴት ልጅ ግርዛት እና ያለዕድሜ ጋብቻ ለማስቆም የማህበረሰብ ንቅናቄና ዘመቻ አካሄደች በ2018 ዓ.ም. ሐምሌ 15 ቀን፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ በተካሄደው የማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ) ከ አማራ ሴቶች ማህበር ጋር በመተባበር እና በዩኒሴፍ (UNICEF) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ፣ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለዕድሜ ጋብቻን መከላከል ላይ ያተኮረ የማህበረሰብ ንቅናቄና ዘመቻ አካሄዳች።ዘመቻው የሀገሪቱን ህጎችና ፖሊሲዎች ከማህበረሰቡ አመለካከትና ባህላዊ ልማዶች ጋር በማገናኘት ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችን ከሥሩ ለመቀየር ያለመ ነበር። ብዙ ሰዎች በሚገኙበት የገበያ ስፍራና የመተላለፊያ አካባቢዎች የተካሄደ ሲሆን ከ3,000 በላይ በስፍራው የተገኙ ገበሬዎች፣ ነጋዴዎች ፤ ህጻናት ፤ እናቶች እና የደባርቅ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎችን በቀጥታ ለማድረስ ተችሏል።በዘመቻው ውስጥ የደባርቅ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት እና ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት በሚደግፉት ዋልያ የባህል ቡድን አባላት በድራማ፣ በግጥም እና በዘፈን የሴት ልጅ ግርዛትን ፣ ያለዕድሜ ጋብቻን እና ሌሎች ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችን በጤና፣ በትምህርት፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ህይወት ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት በሚዳስስ መልኩ አስተማሪ አዝናኝ በሆነ መንገድ አቅርበዋል።በመዝጊያው የማህበረሰብ ንቅናቄና ዘመቻ ላይ ከህፃናት ጋብቻ የተረፉ ህፃናት የህይወት ተሞክሮዎቻቸውን በማካፈል ተሳትፈዋል። በተጨማሪም የሃይማኖት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች የሴት ልጅ ግርዛትና ያለዕድሜ ጋብቻ ከሃይማኖትም ሆነ ከባህል ጋር የማይያያዙ ጎጂ ድርጊቶች መሆናቸውን በይፋ በማረጋገጥ አቋማቸውን ገልጸዋል።የተቀናጀ የተቋማት ትብብርና ጥበቃ ዘመቻው የህዝብ ተሳትፎን ከማሳደግ ባለፈ፣ ከኢ.ሴ.ማ.ቅ ፣ ከአማራ ሴቶች ማህበር ፤ ከወረዳ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት፣ በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ ያሉ አመራሮች እንዲሁም ከአካባቢ የዋች ዶግ (ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችን ተከላካይ ኮሚቴዎች) የተውጣጣ የተቀናጀ የክትትልና የቁጥጥር ቡድን አሳትፏል። የገበያ ቦታው ላይ የተሳታፊዎችን ደህንነት፣ የዘመቻውን ሰላማዊ አፈጻጸም ለማረጋገጥ በወረዳው የተመደቡ አራት የፀጥታ አባላት በሙሉ ጊዜ ጥበቃ አድርገዋል። ይህ የተቀናጀ ተሳትፎ በማህበረሰቡ ውስጥ የሪፖርት ስርዓቶችን በማጠናከር፣ በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች፣ በማህበረሰብ ፖሊስና በሌሎች ተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅት በይበልጥ አጠናክሮል። እንዲሁም ለፆታዊ ጥቃት ተጎጂዎች የሚገኙ የሪፈራል አገልግሎቶችን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለህዝቡ ተሰጥቷል።በተጨማሪም በአካባቢው ቋንቋና አውድ የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶች ለህዝቡ ተሰራጭተዋል። እንዲሁም በዘመቻው የአካባቢ የዋች-ዶግ መዋቅሮች የበለጠ ተጠናክረው የሴቶችና የህጻናት መብትና የአካል ደህንነትን ለመጠበቅ የተቋማት እና የማህበረሰቡ የጋራ ቁርጠኝነት የታየበት ነበር።በነበረው የማህበረሰብ ንቅናቄ ዘመቻም በቀጥታ መረጃውን ከተካፈሉት ማህበረሰብ አባላት በተጨማሪ በተበተኑት በራሪ ወረቀቶች ፤ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ፤ ቲሸርቶች ፤ በተያዙ መፈክሮች አማካኝነት ከ 15,000 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተደራሽ ይሆናል፡፡ 751055821_2123431321928662_5442136175870247809_n 751055824_2123448768593584_6542445057567765018_n 751241499_2123428371928957_758332761417328011_n 751446932_2123430835262044_8052440051326584197_n 751471582_2123423311929463_3220750847336932614_n 751563099_2123422625262865_993027466395301520_n 751563100_2123446161927178_1962717069885023055_n 752334338_2123423038596157_649267776435065624_n 752489214_2123431065262021_6890694986345746908_n 753192792_2123448268593634_4383884209365947411_n Load More End of Content.
የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ) በሴት ልጅ ግርዛት እና ያለዕድሜ ጋብቻ ለማስቆም የማህበረሰብ ንቅናቄና ዘመቻ አካሄደች Read More »

