የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር መጠለያን ጎበኘች

የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር መጠለያን ጎበኘች የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ሰኔ 2/2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር የሴቶች መጠለያ የጎበኘች ሲሆን በጉብኝቱ የኢ.ሴ.ማ.ቅ ቦርድ አባላት እና ሰራተኞች በልደታ ክ/ከተማ የሚገኘውን መጠለያ በስፍራው ተገኝተው ፆታዊ-ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት ችለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ሁለት የሴቶች መጠለያ ያለው ሲሆን እነዚህም በአዲስ ከተማ እና በልደታ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ፡፡ የልደታ ክ/ከተማ የሴቶች መጠለያ እ.ኢ.አ በ2010 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ስራውን ለመጀመር ያነሳሳቸው ዋናው ምክንያት ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ማረፊ አጥተው ለተደራራቢ ችግር ሲጋለጡ በማየታቸው ችግሩን ሙሉ በሙሉ መቅረፍ እንኳን ባይችሉ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲያገኙ እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ታስቦ ቀና ልቦች ባሏቸው አመራሮች እንደተመሰረተ ለማወቅ ችለናል፡፡ በመጠለያው ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ሴቶች ነፍሰ- ጡር ሆነው ወደ መጠለያ የሚገቡና እዛው ልጆቻቸውን እንደወለዱ ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም መጠለያ ውስጥ ያሉ ህፃናት ትምህት የጀመሩ ሲገኙበት አብዛኞች ግን ጨቅላ ህፃናት ናቸው፡፡ በማብራሪቸውም የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ እናታለም እንዳለ እንደተናገሩት መጠለያው ተደራራቢ ችግር ያለበት መሆኑን ገልፀው በዚህም ከእለት ምግብ ጀምሮ የተለያዮ መሰረታዊ ድጋፎችን ፣ የክህሎት ስልጠናዎችን፣ የስነልቦና እና ማህበራዊ ድጋፎችን በተለይ ደግሞ መጠለያው ያለበትን ሁኔታ ማሻሻል ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን በአፅንሆት ገልፀዋል፡፡ ኢ.ሴ.ማ.ቅ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህን እንደገለፁት መጠለያው በመደበኛነት ሊያሟላ የሚገባቸው ነገሮች እንዳሉ በመጥቀስ በዚህም የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ለመጠለያው ድጋፍ እንዲያደርጉ ማህበሩም በዚህ ላይ በሰፊው እንዲሰራበት አስታውሰው ፤ ኢ.ሴ.ማ.ቅ የበኩሏን እንደምትወጣ በመግለፅ የምግብ እና የንፅህና መጠበቅያ መጠነኛ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን መጠለያውም ያለበትን ሁኔታ ለማሻሻል እንዲሁም የሴቶቹን ህይወት በዘላቂነት ለመታደግ የተለዩ ድጋፎችን የሚፈልግ በመሆኑ የሁላችንንም የጋራ ጥረት እንዲታከልበት ኢ.ሴ.ማ.ቅ ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር መጠለያን ጎበኘች Read More »